ራስን መርዳት / Self help (Amharic)

ራስዎ እንዴት እንደሚሰማዎት መረዳት ወይም ምን ሊረዳዎት እንደሚችል ማወቅ አንዳንዴ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። በSolace ውስጥ ስለ ተለያዩ የአእምሮ ጤና እና ደህንነት ርዕሶች ቪዲዮዎችን አዘጋጅተናል፣ እነዚህም ጭንቀት፣ እንቅልፍ፣ አስቸጋሪ ስሜቶች እና ህመምን ያካትታሉ።

እነዚህ ቪዲዮዎች አሁን እያጋጠሙዎት ያሉ አንዳንድ ተሞክሮዎችን ዳዎትሊረ ይችላሉ። እንዲሁም ሊሞክሩዋቸው የሚችሉ ቀላል ሀሳቦችን እና ቴክኒኮችን ያካትታሉ።

ከዚህ በታች ስምንት መግለጫዎችን ያገኛሉ። ከእነሱ ውስጥ ራስዎ እንደሚሰማዎት የሚገልጽ የሚመስልዎትን ማንኛውንም መግለጫ ጠቅ ያድርጉ። ከዚያም ሊጠቅሙዎት የሚችሉ አንዳንድ ቪዲዮዎችን ያያሉ።

ሁሉንም ቪዲዮዎች ማየት አያስፈልግዎትም። ለእርስዎ በጣም ጠቃሚ እንደሆኑ የሚሰማዎትን መምረጥ ይችላሉ።

እንዲሁም ስለ አእምሮ ጤና እና ደህንነት ተጨማሪ ቪዲዮዎችን ለማግኘት የቪዲዮዎቻችንን ዝርዝር ማውጫ መጎብኘት ይችላሉ።

ማውጫውን ለመጎብኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ።

ሊጨነቁ፣ ሊወጠሩ ወይም መዝናናት እንደማይችሉ ሊሰማዎት ይችላል። በአእምሮዎ ውስጥ ብዙ ሀሳቦች እየተመላለሱ ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም በሰውነትዎ ላይ ለውጦችን ሊያስተውሉ ይችላሉ፣ ለምሳሌ ፈጣን የልብ ምት፣ የጠነከሩ ጡንቻዎች ወይም እረፍት የማጣት ስሜት። እነዚህ ስሜቶች ሕይወት አስቸጋሪ፣ ደህንነት የሌለው  ወይም ያልተረጋገጠ  ሊያስመስለው ይችላሉ።

ከታች እነዚህን ስሜቶች ለመቋቋም ሊረዱዎት የሚችሉ አንዳንድ ቪዲዮዎችን ማግኘት ይችላሉ።

ብዙ ጊዜ ሐዘን፣ ዝቅተኛ ስሜት ወይም ከባድነት ሊሰማዎት ይችላል። ጉልበትዎ ሊቀንስ ይችላል ወይም ከዚህ ቀደም ደስ በሚያሰኙዎትን ነገሮች መደሰት ከባድ ሊሆንብዎት ይችላል። እንዲሁም ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚያሳልፉትን ጊዜ መቀነስ ሊፈልጉ ይችላሉ። እነዚህ ስሜቶች ከአስቸጋሪ ልምድ፣ ከማጣት (ኪሳራ) ወይም ከረዥም ጊዜ ውጥረት በኋላ ሊከሰቱ ይችላሉ።

ከታች ያሉት ቪዲዮዎች ይህንን ችግር እንዲረዱት እና እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል ለመረዳት ሊረዱዎት ይችላሉ።

አንዳንድ ጊዜ ከራስዎ፣ ከሌሎች ሰዎች ወይም ከዙሪያዎ ካለው ዓለም የራቁ እንደሆኑ ሊሰማዎት ይችላል፤ ምንም እንኳን ከእነሱ ጋር ኣብረው ቢኖሩም። ነገሮች እንግዳ፣ የራቁ ወይም እውነተኛ ያልሆኑ ሊመስሉዎት ይችላሉ። በዙሪያዎ ምን እንደሚከሰት ማስተዋል አስቸጋሪ ሊሆንብዎት ይችላል። ይህ በተለይ በጣም አስጨናቂ ወይም አስፈሪ ነገር ካጋጠምዎት በኋላ ሊከሰት ይችላል።

ከዚህ በታች ያሉት ቪዲዮዎች እነዚህን ስሜቶች እንዲረዱ እና ለመቆጣጠር ሊረዱ የሚችሉ አንዳንድ መንገዶችን እንዲሞክሩ ሊያግዙዎት ይችላሉ።

እንቅልፍ ለመውሰድ ወይም ተኝተው ለመቆየት አስቸጋሪ ሊሆንብዎት ይችላል። በሌሊት መካከል ሊነቁ ወይም ከፈለጉት በፊት ሊነሱ ይችላሉ። እንዲሁም ለመተኛት ሲሞክሩ አእምሮዎ በብዙ ሀሳቦች የተሞላ እንደሆነ ሊሰማዎት ይችላል። ጭንቀት፣ ስጋት እና አስቸጋሪ ተሞክሮዎች ሁሉ በእንቅልፍዎ ላይ ተጽእኖ

ሊያሳድሩ ይችላሉ።  ከዚህ በታች ያሉት ቪዲዮዎች አሁን እያጋጠሙዎት ላሉት ችግሮች ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ።

በሰውነትዎ ውስጥ ህመም፣ መጥበብ ወይም ሌሎች የማይመቹ ስሜቶች ሊኖሩዎት ይችላሉ። ጭንቀት እና አስቸጋሪ ተሞክሮዎች በአእምሮ ብቻ ሳይሆን በሰውነትም ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።

በተጨማሪም ህመም ወይም አለመመቸት የበለጠ ጠንካራ ወይም ከባድ ስሜት እንዲሰማዎት ሊያደርጉ ይችላሉ።

ከታች ያሉት ቪዲዮዎች ሊረዱዎት የሚችሉ መረጃዎችን እና ምክሮችን ይሰጣሉ።

አስቸጋሪ ትዝታዎች ምንም እንኳን ማሰብ ባይፈልጉም ወደ አእምሮዎ ተመልሰው ሊመጡ ይችላሉ። በቀድሞ የተከሰቱ ነገሮችን ደጋግመው ማሰብ ሊቀጥሉ ይችላሉ። እንዲሁም የሚያስጨንቁ ምስሎች፣ መጥፎ ሕልሞች ወይም አስፈሪ ቅዠቶች ሊኖሩዎት ይችላሉ። ይህም ከአስፈሪ ወይም በጣም አስቸጋሪ ተሞክሮዎችን ካሳለፉ በኋላ ሊከሰት ይችላል።

ከዚህ በታች ያሉት አንዳንድ ቪዲዮዎች እነዚህን ተሞክሮዎች ለመቋቋም ሊረዱዎት ይችላሉ።

ትኩረት ማድረግ፣ ነገሮችን ማስታወስ ወይም በአንድ ነገር ላይ አተኩረው መቆየት አስቸጋሪ ሊሆንብዎት ይችላል። አእምሮዎ በብዙ ሀሳቦች የተሞላ እንደሆነ ሊሰማዎት ይችላል፣ ወይም ሀሳቦችዎ ከአንድ ነገር ወደ ሌላ በቀጣይነት ሊዘዋወሩ ይችላሉ። ጭንቀት፣ ስጋት፣ የእንቅልፍ እጥረት እና አስቸጋሪ ተሞክሮዎች ሁሉ ትኩረት ማድረግን የበለጠ አስቸጋሪ ሊያደርጉት ይችላሉ።

።ይህንን ችግር ለማገዝ ከዚህ በታች ያሉትን ቪዲዮዎች ማየት ይችላሉ።

ነገሮች ሊሻሻሉ እንደሚችሉ ማመን አስቸጋሪ ሊሆንብዎት ይችላል። የበለጠ ተስፋ እንዲሰማዎት ወይም በነገሮች የበለጠ ደስታ ለማግኘት ሊፈልጉ ይችላሉ። ከአስቸጋሪ ተሞክሮዎች ወይም ከረዥም ጊዜ ውጥረት በኋላ፣ አዎንታዊ ስሜቶችን ማስተዋል የበለጠ ከባድ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ትንሽ የምቾት፣ የደስታ ወይም የግንኙነት ጊዜያት አሁንም አስፈላጊ ሊሆኑ ይችላሉ።

ከዚህ በታች ያሉት አንዳንድ ቪዲዮዎች ጠቃሚ ሆነው ሊያገኟቸው ይችላሉ።